Entries by Website Team

በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በጀርመን ድሶልዶርፍ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሙሴ ሚያዚያ 16 ቀን 2008 ዓ.ም. በእለተ ሆሳዕና ተባርኮ ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ።

ሀገረ ስብከቱ የመጀመሪያውን “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ መርሐግብር አካሄደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ግንቦት 20 ቀን 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ አባት የሆነውን ቅዱስ ያሬድን ሕይወቱን እና ሥራዎቹን የሚዘክር “ዝክረ ቅዱስ ያሬድ“ የተሰኘ መርሐግብር በጀርመን ካርልስሩኸ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ከግንቦት 12-14 2008 ዓ.ም. በደማቅ ስነ ሥርዓት […]

ትንሣኤ

በዲ/ን ብሩክ አሸናፊ ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ […]

የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሔደ

በጀርመን ን/ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል ሚያዚያ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ የግብጽ ገዳም ከሚያዝያ 7- 9 ቀን 2008 ዓ.ም አካሔደ። ሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ.ም የመርሐ ግብሩ የመጀመሪያ ቀን የካርስሩህ ምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የክሮንበርግ […]

ኒቆዲሞስ

፩ መግቢያ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ። እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ […]

“ኦ ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ” ማቴ. ፳፭፥፳፫።

በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር ይባላል። ገብር ኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው አስተምሯል። ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐቢይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብር ኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ኄር ጥቂት […]

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ደብረዘይት የዓቢይ ጾም እኩሌታ ነው ። በእለቱም ስለ ዳግም ምጽአት ይነገራል። ስለ ምጽአት ነቢዩ ዘካርያስ «በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉ…አምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል…አንድ ቀን ይሆናል…. በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር […]

መጻጒዕ (ዮሐ. ፭፥፲፫)

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓ.ም የነፍሳችንን ማሠሪያ እንዲፈታና ዓለሙን ከተያዘበት የኃጢአት በሽታ እንዲያድን ለቤዛነት፤ እንዲሁም የመልካምና የበጎ ምግባራት ሁሉ አብነት ሆኖ በሥራና በቃል እንዲያስተምር ወዳለንባት ምድር በሥጋ ቅድስት ድንግል ማርያም ወረደ ተወለደ:: ቤተክርስቲያናችን በአራተኛው የዓቢይ ጾም ሳምንት እግዚአ ለሰንበት ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ“ቤተሳይዳ” የፈጸመውን ተአምራት መጻጒዕ ብላ ሰይማ ታስበዋለች። […]

ምኵራብ

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ድህረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ ማርያም በተዋህዶ ከበረ።“ይደልዎነ ንእምን ከመ ቦቱ […]

ዘወረደ

በዲያቆን ስመኘው ጌትዬ የካቲት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እንኳን ለዓቢይ ጾም በሰላም አደረሰን። የ፳፻፰ (2008) ዓ.ም ዓቢይ ጾም የካቲት ፳፰(28) ቀን ተጀምሮ ሚያዝያ ፳፫ (23) ቀን ይፈጸማል። ይህ ጾም በ 8 ታላላቅ ሳምንታት የተከፋፈለ ሲሆን እነርሱም ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኲራብ፣ መጻጒዕ ፣ ደብረዘይት፣ ገብርኄር፣ ኒቆዲሞስ፣ እና ሆሳዕና ይባላሉ፡፡ በዚህ ጾም ውስጥ በአጠቃላይ ጾመ እግዚእነ (የጌታችን ጾም) […]