የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሔደ
በአውሮፓ ማእከል ኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል
ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ፲፮ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከሐምሌ ፩-፫ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም በስዊድን አገር ስቶክሆልም ከተማ ተካሔደ።
በጠቅላላ ጉባኤው በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ከሰባ በላይ የማእከሉ አባላት፤ የዋናው ማእከልና የሰሜን አሜሪካ ማእከል ተወካዮች፤ እንደዚሁም ጥሪ የተደረገላቸው ካህናትና ምእመናን ተሳትፈዋል።

በማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል የጀርመን ንዑስ ማእከል 3ኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን ክሮፍልባህ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ እንጦስ

