Entries by Website Team

አዳም እና ሔዋን (ለልጆች) (ዘፍ 1፣2፣3)

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? በአለፈው በቀረበው ክፍለ ትምህርት እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው ፍጥረታት እንዳነበባችሁና እንደተረዳችሁ ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ እግዚአብሔር በስድስተኛው ቀን ስለፈጠራቸው አዳም እና ሔዋን እንደሚከተለው ቀርቦላችኋል። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ከፈጠረለት በኋላ በስድስተኛው ቀን ዐርብ የመጀመርያውን ሰው አዳምን ፈጠረ። እግዚአብሔር ሲፈጥረውም በእራሱ መልክ እና ምሳሌ ፈጠረው፤ በምድር ላይ ለሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ ገዢ አደረገው። […]

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፤ (መዝ 64፥ 11)

ዲ/ን  ውብዓለም  ደስታ  ጳጉሜን 04 ቀን 2005 ዓ.ም.  ዘመን የሚለወጥበት የመስከረም ወር ዘር ዘርተው ተክል ተክለው የሚኖሩ ሐረስተ ምድር በክረምት የዘሩትን ዘር አሽቶ አፍርቶ ምድርም በልምላሜ ተጊጣ እንስሳትም ለምለሙን ሣር ግጠው ጽሩውን ውኃ ተጎንጭተው ጠግበው አምረው የሚታዩበት የልምላሜ የፍሬ ወር ነው። “ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ እንዲሁ […]

የደቡብ፣ የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ

ጳጉሜን 02 ቀን 2005 ዓ.ም.   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ የደቡብ ምሥራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀ/ስብከት ከነሐሴ 24 – 25፣ 2005 ዓ.ም በጀርመን ሀገር በሚገኘው የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ እንጦንስ ገዳም ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ፡፡ በዕለቱም ብፁዕ አቡነ ሙሴ የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖደስ አባል፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤያት እና የመንፈሳዊያት ማኅበራት ተወካዮች በአባልነት ተገኝተዋል፡፡ ጉባኤው በብፁዕነታቸው […]

“ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ” (መኃ 2፡10)

ዲ/ን ውብዓለም ደስታ  ከኔዘርላንድስ ቀጠና ማዕከል  ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.   ከላይ በርዕሱ እንደተገለጸው ከመዝሙር ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ሰሎሞን እመቤታችንን እንዲህ ብሏታል፡፡ «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ÷ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ ÷ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ […]

ሥነ-ፍጥረት/ለልጆች

ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም.  ልጆች እግዚአብሔር አምልካችን ሰማይ እና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው የሚኖሩትን ፍጥረታትን መቼ እንደፈጠራቸው ታውቃላችሁ? በዚህ ጽሁፍ ስለ ሥነ-ፍጥረት ትማራላችሁ። እግዚአብሔር ፍጥረታትን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ የሁሉ ፈጣሪ ነው። እግዚአብሔርም በሳምንት ውስጥ ካሉ ሰባት ቀናት (ዕለታት) በመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት የተለያዩ ፍጥረታትን ፈጠረ።      

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

መግቢያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ ጊዜ ካህናት እና ምእመናን የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት በተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ድርሻቸውም ምን እንደሆነ ያስተምራቸው ነበር:: ለምሳሌ የመንፈስ ልጁ የሆነ ቅዱስ ጢሞቴዎስን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲህ በማለት መክሮታል:-“በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ […]

እንደተናገረ ተነሥቷል (ማቴ28፥5)

እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። በአባ ወልደትንሣኤ ጫኔ ሚያዚያ 26፣ 2005ዓ.ም. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድህነት ሲል ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና […]

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም.     የዓለሙ ፍጻሜ ምልክቱ ምንድ ነው?/ማቴ. 24፣3/   በዓቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት ደብረ ዘይት 5ኛው ሳምንት ላይ ይውላል፡፡ ደብረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ ዛፍ ተራራ ማለት ሲሆን፣ ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ ቅዱሳን ሐዋርያት” የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?”/ማቴ. 24፣3/ ብለው ጠይቀውት እርሱም የማይቀረውን […]

መንፈሳዊ ሕይወትና ስደት

በይበልጣል ጋሹ የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. የዚህ አጭር ጽሁፍ ዓላማ በተለያየ ምክንያት በስደት ለምንኖር የቦታ መቀየር ተፅዕኖ ሳያሳድርብን በሃይማኖታችን ጸንተን እስከመጨረሻው በመንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖርና እግዚአብሔር አምላክ ሁልጊዜ ከስደተኞች ጋር መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ተገንዘበን “እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል” መዝ 145፡9 የሚለውን ህያው ቃል በውስጣችን አስቀምጠን የሚመጣብንን ፈተና ሁሉ በእግዚአብሔር እንደምንወጣው ለማስረዳት ነው። ነብዬ እግዚአብሔር ቅዱስ […]

የ6ኛው ፓትርያርክ ሥርዓተ ሢመት ተፈጸመ

የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሥርዓተ ሢመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ተፈጸመ፡፡ ከዋዜማው ጀምሮ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የማኅሌት ጸሎት በማድረስ የተጀመረው ሥርዓተ ጸሎት ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከአቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ […]