«የአክለክሙ መዋእል ዘሃለፈ ፥ ያለፈው ዘመን ይብቃችኋል» ቅዱስ ያሬድ እና ፩ኛ ጴጥሮስ ፬ ፥ ፫- ፬

በመጋቢ ሀዲስ ምስጢረ ስላሴ ማናየ

ጳጉሜን  ፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. 

«የአክለክሙ መዋእል ዘሃለፈ ፥ ያለፈው ዘመን ይብቃችኋል» ቅዱስ ያሬድ እና ፩ኛ ጴጥሮስ ፬ ፥ ፫- ፬

በቅድሚያ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ያሸጋገረን፤ በመግቦቱ ያልተለየን፤ በችርነቱ የጠበቀን፤ በምህረት አይኖቹ የተመለከተን፤ በብርቱ ክንዶችሁ የደገፈን፤ የዘመናት ባለቤት የፈጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ለዚህ ኣመት ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ይድረሰው አሜን።

በቸር አድረን የምንውለው፤ ተኝተን የምንነሳው፤ ሰርተን የምናገኘው፤ ደክመን የምንበረታው፤ ታመን የምንደነው፤ ወድቀን የምንነሳው፤ ከቸርነቱ ከጠባቂነቱ የተነሳ ነው። እግዚአብሔር አምላካችን ሰውን ከድንጋይ እና ከእንጨት ለይቶ በደማዊት ነፍስ ከእንስሳት እና ከአራዊት ለይቶ በህያው ነፍስ አክብሯታል በአርያው እና በአምሳሉም ፈጥሯታል። «ወገብሮ እግዚአብሔር ለእጓለ እመህያው እመሬተ ምድር በአሪያሁ ወበአምሳሊሁ ፤ እግዚብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአርያውና በአምሳሉም ፈጠረው» ዘፍ ፩፥፪፮

Read more

በክርስቶስ በኲርነት ኹላችን እንነሣለን (፩ኛ ቆሮ፲፭፥፳-፳፪)

በዲ/ን ሰሎሞን አስረስ

ሚያዚያ 11 ቀን 2006 ዓ.ም. 

እግዚአብሔር ሰውን እንደ መላእክት ሕያው ስሙን ሊቀድስ ክብሩን እንዲወርስ እንጂ እንዲታመም እንዲሞት አድርጎ አልፈጠረውም ነበር፡፡ ሞት ግን ሰው በፈቃዱ ያመጣው እንጂ እግዚአብሔር ሰውን ሊሞት አልፈጠረውም ። ጥበበኛው ሰሎሞን ‹‹በሕይወታችሁ ስሕተት ለሞት አትቅኑ፤ በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ፡፡ እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና፤ የሕያዋንም  ጥፋት ደስ አያሰኘውምና፡፡ ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረቱን ፈጥሮአልና፡-የዓለም መፈጠርም ለድኀነት ነውና በእነርሱም ዘንድ የጥፋት መርዝ አልነበረምና ለሲኦልም በምድር ላይ ግዛት አልነበረውምና፡፡ ጽድቅ አትሞትምና፡፡ ክፉዎች ግን በእጃቸውና በቃላቸው ጠሩት፤ ባልንጀራም አስመሰሉት፡፡ በእርሱም ጠፋ፡፡›› እንዲል። (ጥበብ ፩፥፲፪-፲፯)::

Read more

የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 24፡4)

መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. 

መ/ር ሰሎሞን መኩሪ 

በቅዱስ ወንጌል የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? (ማቴ 244) የጠየቁ የእጁን ተአምራት ተመልክተው የቃሉን ትምህርት ሰምተው ሁሉን ትተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዋለበት የዋሉ ካደረበት ያደሩ ትምህርት ተአምራት ያልተከፈለባቸው ቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት ናቸው፡፡ ርሱም የተናገራቸውን ሰምተው ለብቻቸው ሲሆኑ በሚያድሩበት በደብረዘይት ተራራ ላይ ጌታ ሆይ ንገረን ይህ መቼ ይሆናል የመምጣትህና የዓለሙ ፍፃሜ ምልክቱ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁት በዚህ ክፍለ ንባብ ሐዋርያት ሶስት ነገሮችን ጠይቀውታል፡፡

Read more

ዓቢይ ጾም

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ.ም.

በአባ ዘሚካኤል ሬሳ 

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ለመጾም አደረሳችሁ!!!

ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ። አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ጾመ። ከዛም ፈታኝ ዲያብሎስ ቀርቦ በስስት፣ በትእቢትና በፍቅረ ነዋይ ፈተነው። ጌታችንም ፈተናዎቹን በጥበበ አምላክነቱ ድል በማድረግ ድልን ለአዳምና ለእኛ ለልጆቹ ሰጠን (ማቴ. 4፡ 1 – 11)

በቤተ ክርስቲያናችን የትምህርተ ጾም አስተምህሮ መሰረት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾመ ሁዳዴ ትልቁን ስፍራ ይይዛል። ይህም የቀደመው አዳም በጾም ግድፈት ምክንያት ማለትም አትብላ የተባለውን በመብላት ወድቆ፣ተዋርዶ፣ ኃይሉን አጥቶ፣ ዲያብሎስ ሰልጥኖበት፣ ስጋ ፈቃድ አይሎብት፡ የዓለም አምሮት ማርኮት ሞትና የሞት ሞት ሰልጥኖበት ነበረ። ነገር ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ተወልዶ፣ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ፣ ሰው በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር አረጋግጦ፣የአዳም ጾም መሻርና የመዋረዱን ክስረት ለመካስ ጌታም ይህን ጾም በመጾም የአዳምን ክብረት መልሶለታል

Read more

እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ (ራእ ፪፡፳፭)

በዲ/ን ሰሎሞን መኩሪያ 

ጥቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም. 

ይህንን ይለ ቃል የተናገረው ቅዱስ እግዚአብሔር በሐዋርያዉና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ማካነው። ቅዱስ ዮሐንስ ከዓሣ አጥማጅነት ከተጠራበት ጊዜ አንስቶ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀል ስ ተከተሎታል፤ በዚያም የጌታችንን መከራ እየተመለከተ ቢያዝንና ቢያለቅስ ይጽናና ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እን እናትህ በማለት የእናትነት ቃል ኪዳን ተቀብሏል። እርሷንም ወደ ቤቱ ወስዶ ፲፭ ዓመት ታጥቆ ልግሏታል።

ስብከተ ኤፌሶን ሂዶ በዚ ወንጌልን ለማስተማር ከጣዖት አምላኪው ንጉስ ድምጥያኖስ ብዙ መከራ ተቀብሏል። በዚያም ለነበሩ ምእመናን የሃይማኖት ጽናትንና መከራ በመቀበል ያስተማረ ሰባት አብያተ ክርስትያናትን ከመሠረተ በሁዋላ ከንጉስ ድምጥያኖስ ግዞት ተፈርዶበት ፍጥሞ ወደ ምትባል ደሴት ግዞ በዚያም በምድርና በሰማይ ያለውን ወደፊትም የሚደረገውን ነገር በራእይ ተገልጾለት ጽፏል። ላም ፺፱ ዓመቱ ሞትን ሳያይ የተሰወረ የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ቅዱስ ነው። (ማቴ፲፱ ዮሐ ፲፱፳፮ ዮሐ ፳፩፳፬)

Read more

ወወሃብኮሙ ትእምርት ለእለ ይፈርሁከ፣ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው (መዝ 59፡4)

በመምህር ሰሎሞን መኩሪያ

መስከረም  16 ቀን 2006 ዓ.ም.

ይህንን የተናገረ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ከተሰጡት 7 ሃብታት አንዱ ሃብትንቢት  ነው በዚተሰጠው ሃብ ትንቢት  የራቀው ቀርለታል የቀረበው ከናውኖለታልየረቀቀው ጐልቶለታል ስለዚህም ከእርሱ በፊት የተደረገውን፣ በእርሱ ዘመን የሆነውን፣ ከእርሱም በኋላ እስከ እለተ ምፅአት የሚደረገውን ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ገልፆለት ብዙ ነገር ተንብይዋል። ትንቢቶቹም መካከል አንዱ የመስቀሉ ነገር ነው፡፡

ቅዱስ መስቀል እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሃ ፈሳሽ  ሳይሆን ትንቢት ሲነገርለት ምሳሌ ሲመሰልለት የኖረና በኃላም በከበረ በክርስቶስ ደም ተቀድሶ የመለኮት ዙፋን ሆኖ የተመረጠ ለክርስቲያኖች ኃይልና መመኪያ እንዲሁም አጋንንትን ድል መንሻ ነው፡፡

Read more

ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፤ (መዝ 64፥ 11)

/  ውብዓለም  ደስታ 

ጳጉሜን 04 ቀን 2005 ዓ.ም. 

ዘመን የሚለወጥበት የመስከረም ወር ዘር ዘርተው ተክል ተክለው የሚኖሩ ሐረስተ ምድር በክረምት የዘሩትን ዘር አሽቶ አፍርቶ ምድርም በልምላሜ ተጊጣ እንስሳትም ለምለሙን ሣር ግጠው ጽሩውን ውኃ ተጎንጭተው ጠግበው አምረው የሚታዩበት የልምላሜ የፍሬ ወር ነው። “ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥ ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ እንዲሁ ታሰናዳለህና። ትልምዋን ታረካለህ፥ ቦይዋንም ታስተካክላለህ፤ በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥ ቡቃያዋንም ትባርካለህ። በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ። መዝ (64 (65)፥ 9-13)

Read more

“ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ” (መኃ 2፡10)

ዲ/ን ውብዓለም ደስታ 

ከኔዘርላንድስ ቀጠና ማዕከል 

ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. 

wodaje hoy tenesh

 ከላይ በርዕሱ እንደተገለጸው ከመዝሙር ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ሰሎሞን እመቤታችንን እንዲህ ብሏታል፡፡ «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ÷ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ ÷ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡» (መኃ.2-10-14)፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ሲተረጎም በውስጡ ብዙ ምስጢራዊ ነገሮችን ያቀፈ ነው፡፡ «በክረምትና በዝናብ» የተመሰሉ የእመቤታችን መከራዎች ናቸው፡፡ የመከራሽ ጊዜ አልፏል ሲላት «አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ» ማለቱ ከልጅሽ እግር ሥር ቁጭ ብለው ተምረው ወንጌልን የተቀበሉ ሐዋርያት አንቺን በእናትነት የተረከቡ የሐዋርያት ድምፅ ወይም ስብከት በምድር ሁሉ መሰማቱን ያጠይቃል፡፡

Read more

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

መግቢያ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ ጊዜ ካህናት እና ምእመናን የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት በተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ድርሻቸውም ምን እንደሆነ ያስተምራቸው ነበር:: ለምሳሌ የመንፈስ ልጁ የሆነ ቅዱስ ጢሞቴዎስን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲህ በማለት መክሮታል:-“በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው::” (1ጢሞ 3፥15)

Read more

እንደተናገረ ተነሥቷል (ማቴ28፥5)

እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።

በአባ ወልደትንሣኤ ጫኔ

ሚያዚያ 26 2005ዓ.ም.

Easterጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድህነት ሲል ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በጲላጦስ ካለበደሉ ከወንበዴዎች ጋር ተፈርዶበት፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ አዳምንና ዘሩን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መልሶ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብርሃንን ተጎናጽፎ  በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል።

Read more