በሀገረ ጀርመን በርሊን ከተማ የቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ
ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የተገዛው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ተከበረ፡፡
ዜና
ግንቦት 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ፣ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የበርሊን ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን የተገዛው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓ.ም ተከበረ፡፡
በጀርመን ቀጣና ማእክል
ግንቦት 20 ቀን 2007 ዓ.ም.
በማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማእከል ግንቦት ፲፭ እና ፲፮ ፳፻፯ ዓ.ም. በጀርመን ሙኒክ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ”ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የድርሻችንን እንወጣ” በሚል ርዕስ የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አካሄደ::
ግንቦት 19 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ፲፭ኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ሊያካሂድ ነው። ከሰኔ ፳፮ እስከ ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም. በሚቆየው በዚህ ጉባዔ፦
ሚያዚያ 04 ቀን 2007 ዓ.ም.
የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅ እና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ የትንሣኤን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
በአውሮፓ ማዕከል መገናኛ ብዙኀን እና ቴክኖሎጂ አገልግሎት ክፍል
መጋቢት 16 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል አዘጋጅነት የሐዊረ ሕይወት (የሕይዎት ጉዞ) መርሐ ግብር ከመጋቢት 11 እስከ 13 /2007ዓ.ም በክሩፈልባክህ (Kroeffelbach) ከተማ በሚገኘው በቅዱስ እንጦንስ የግብፅ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የመጡ ከ200 በላይ ምዕመናን ተሳትፈውበታል::
የጉባኤው ተሳታፊዎች አርብ ምሽት 1 ሰዓት ተኩል ላይ ከፍርንክፈረት 64.5 ኪ.ሜ ላይ እርቀት በሚገኘው የቅዱስ እንጦንስ የግብፅ ገዳም የተገኙ ሲሆን፤ የገዳሙ አባቶችም የመጣውን እንግዳ በትህትና በመቀበልና ለሁሉም የማረፊያ ቦታ ሰጥተዋል።
መጋቢት 10 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ የ፳፻፯ ዓ.ም. የመጀመሪያውን የገጽ ለገጽ ስብሰባ በዴንማርክ ሀገር በኮፐንሀገን ከተማ በቅዱስ ማርቆስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመጋቢት ፬-፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አካሄደ።
የሥራ አስፈጻሚ አባላቱ አርብ መጋቢት ፬ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ኮፐንሀገን ከተማ የተገኙ ሲሆን፣ ምሽቱን ከዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ አባላት ጋር የጋራ የጸሎት መርሐ ግብር በማድረግ ስብሰባውን ጀምረዋል። ከጸሎቱ በመቀጠል በዴንማርክ የደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ደሬሳ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አጭር ቃለ ወንጌልና ምክር ሰጥተዋል። በመቀጠልም የማዕከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን ሰሎሞን አስረስ የስብሰባውን አላማ ሲገልጹ ሥራ አስፈጻሚ አባላቱ በተለያዩ ሀገራት ሆነው በስካይፕና በስልክ ከሚያደርጉት ስብሰባ በተጨማሪ አባላቱ በአካል ተገናኝተው የበለጠ ተግባብተውና ተቀራርበው አገልግሎቱን ለማፋጠን እና የማእከሉን ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ለመገምገም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማመላከት ይረዳል በሚል ታሳቢነት መሆኑን ገልጸዋል።
በጀርመን ቀጣና ማዕከል
መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት በአይነቱ ልዩ የሆነ እና የሰበካ ጉባዔ አባላትን አቅም ለማሳደግ የታለመ ሥልጠና በሀገረ ጀርመን በፍራንክፈርት ዙርያ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መቀመጫ በሆነው በሩሰልስሀይም ከተማ የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፯ዓ.ም ሰጠ::
የሥልጠና መርሐግብሩን በጸሎትና በቡራኬ የከፈቱት ብፁዕ አቡኑ ሙሴ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ሲሆኑ የስልጠናውን ወቅታዊነት እና አስፈላጊነት አበክረው ተናግረዋል:: በመቀጠልም የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊና የስልጠናው ዋና አስተባባሪ የሆኑት መጋቤ ምሥጢር ኅሩይ ኤርሚያስ የእለቱን መርሐግብር በዝርዝር በማስተዋወቅ እና ጥሪውን አክብረው የመጡ ሰልጣኞችን በማመስገን ስልጠናውን አስጀምረዋል::
በዩኬ ቀጠና ማዕከል
ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
የ፪፻፯ ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በታላቋ ብሪታኒያ በለንደን እና በሊቨርፑል ከተሞች በህብረት ይከበራል። በዓሉ በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት አዘጋጅነት ጥር ፲ እና ፲፩ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ጥር ፲፭ እና ፲፮ ቀን ፪፻፯ ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የለንደን ውጭ ወረዳ ቤተ ክህነት አዘጋጅነት በታላቁ የሊቨርፑል ካቴድራል በደማቅ ሥነ ሥርዓት ይከበራል።
ታህሣስ 28 ቀን 2007 ዓ.ም.
የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የልደትን በዓል አስከመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉትን መልእክት ከዚህ በታች ይመልከቱ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
ታህሣስ 26 ቀን 2007 ዓ.ም.
በኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ.ሰ.ማ.መ.ማኅበረ ቅዱሳን የጀርመን ቀጠና ማዕከል ሁለተኛውን የሐዊረ ሕይዎት ጉዞ ከመጋቢት 11 – 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ወደ ጀርመን ሀገር የሚገኘው ግብጽ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በዚህ መርሐ ግብር ላይ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌል እንዲሁም ከምዕመናን ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ይሰጥበታል። በጉዞው ላይ ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሚመጡ ምዕመና እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ቀጠና ማዕከሉ ለህዝበ ክርስቲያኑ በጉዞው ላይ በመሳተፍ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲመገቡና በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወንድሞች እና እህቶች የሚደረገውን የምክርና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እንዲደግፉ ጥሪውን አስተላልፏል።
ኢሜይል አድራሻ ፡
europe@eotcmk.org / eu.pr@eotcmk.org
ድረገጽ:
www.eu.eotcmk.org