ምኵራብ

ዲያቆን አለባቸው በላይ

የካቲት 25 ቀን 2009 ዓ.ም

 

ቅዱስ ወንጌል እንደሚነግረን በምኵራብ ያገለግሉ ዘንድ የተሾሙ ካሕናተ አይሁድ እና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ኃላፊነታችውን ረስተው፣ዓላማችውን ዘንግተው ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቤት መንፈሳዊ ገበያነቱ ቀርቶ የሥጋ ገበያ፤ ቅጽረ ምኵራብን የወንበዴዎች መናኻሪያ (ማቴ 21:13፤ ሉቃ19:46) አድርገውት ነበር። በዚህ ምክንያት በቤቱ ተገኝቶ ጸሎት ማድረስ፤ መባእ ማቅረብ፤ ከፈጣሪ ጋር መገናኘት የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። ስለዚህ ነው አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በምኵራብ ተገኝቶ ካህናቱን እና ሻጭ ለዋጮችን በመገሰጽ፤ በመግረፍ፤ ገበያውን በመበተን ቤቱን ያነጻውና ክብርና ልዕልናዋን በተግባር ያስተማረው። Read more

ቅድስት

ዲያቆን መስፍን ኃይሌ

የካቲት 18 ቀን 2009 ዓ.ም


የቤተክርስትያናችንን መዝሙር ንባቡን ከዜማው አስማምቶ አጠናክሮ ያስተላለፈልን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው በዓ ጾም ለሚገኙትን እሑዶች ሁሉ የተለየ መዝሙር ስለሠራላቸው እያንዳንዱ እሑድ በመዝሙሩ ስም ይጠራል በዚህም መሰረት የዚህ ታላቅ ጾም ሁለተኛው እሑድ ቅድስት ተብሎ ተሰይሟል። ቅድስት የሚለው ቃል ግሱቀደሰሲሆን ለየ አከበረ መረጠ የሚል ትርጉም ይይዛል። ቅድስት ማለት የተየች የተመረጠች የከበረች ማለት ነው። ቅዱስ የሚለው ቃል እንደ የአገባቡ ለፈጣሪም ለፍጡርም ያገለግላል። ለፈጣሪ ሲነገር እንደ ፈጣሪነቱ ትርጉሙ ይሰፋል ይጠልቃል ለፍጡር ሲነገር ደግሞ እንደ ፍጡርነቱ እና እንደ ቅድስናው ደረጃ ትርጉሙ ሊወሰን ይችላል። እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንል የባህሪ የሆነ ፣ኃጢአት የማይስማማው ፣ለቅድስናው ተወዳዳሪ ካካሪ የሌለው፣ ወደር የማይወጣለት ፣ዘለዓለማዊ የሆነ ማለታችን ሲሆን ፍጡራንን ግን ቅዱሳን ስንል ቅድስናቸው የጸጋ የሆነ ፤ከእግዚአብሔር ያገኙት ፤እንደነጭ ልብስ ጽድቁም ኃጢአቱም እንደ ዝንባሌአቸው የሚስማማቸው፤ ለቅድስናቸው ማዕረግ ደረጃ የሚወጣለት እንደ ገድል ትሩፋታቸው መጠን ሊጨምርም ሊጎድልም የሚችል ማለታችን ነው። ከፍጡራን መካከል ለእግዚአብሔር የተለዩ ሁሉ በጸጋ የቅድስናው ተሳታፊ ሊሆኑ ይችላሉ። መላእክት፣ ሰዎች፣ መካናት፣ ዕለታት ፣አልባሳት፣ ንዋያት ሁሉ ለእግዚአብሔር እስከ ተለዩ ድረስ ከቅድስናው በረከት ይሳተፋሉ እንደ የደረጃቸው ቅዱሳን ተብለው ይጠራሉ።

Read more

ጥር​ ​፳፩​ ​የእመቤታችን​ ​በዓለ​ ​ዕረፍት (​አስተርእዮ​ ​ማርያም)

በቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን

ጥር 20 ቀን 2009 .

” አስተርእዮ ማርያም “

አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል። Read more

ሠለስቱ ደቂቅ በትውልድ መካከል

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ

ታኅሣሥ 18 ቀን 2009 .

ትውልድ ያልፋል ትውልድ ይመጣል። ያልፈው ትውልድ እንደ እምነቱ እና እንደስሥራው ወይ ገነት ወይ ሲዖል ይኖራል። አዲሱ ትውልድ እንዲሁ የዚህን ዓለም ኑሮ ጊዜው ባመቻቸለት ሁኔታ ለሚቀጥለው ዘላለማዊ ሕይወት ወይ ለመንግስተ ሰማያት ወይ ለገኃነመ እሳት እራሱን ያዘጋጃል። ነገር ግን በትውልድ መካከል ሁልጊዜም እግዚአብሔር እንደትውልዱ የእምነት ፍላጎትና ጽናት መጠን ራሱን ይገልጻል። እንደሠለስቱ ደቂቅ ያለምንም አማራጭ በርሱ ሲተማመኑና እራሳችውን ከማንም በላይ ለርሱ አሳልፈው ሲሰጡ እግዚአብሔር አብሮአቸው መሆኑን ያረጋግጣል። እሱ ማንንም አሳፍሮ አያውቅም። ስለዚህም በነነቢዩ ዳንአልና ሠለስቱ ደቂቅ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳአል ትውልድ ዘመን እግዚአብሐር በድንቅ ተአምራቱ በቅዱስ ገብርአል አሳይቶ ነበር። Read more

ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ

በ ዲ/ን አረጋ ጌታነህ

ጥቅምት 25 ቀን 2009 .

“ጽጌ አስተርአየ በውስተ ምድርነ ጊዜ ገሚድ በጽሐ  ፤ አበባ በምድራችን ታየ  የመከርም ጊዜ ደረሰ”  መኃ ፪፥፪

በቤተ ክርስቲያናችን የዘመን አቆጣጠር መሠረት አሁን ያለንበት ወቅት ዘመነ መፀው ይባላል። አንዳንዶች በስሕተት ፀደይ ሲሉት ይሰማሉ። ዓመቱን ለዐራት የሚካፈሉት ወቅቶች በሐዲስ ኪዳን በዐራቱ ወንጌላውያን የሚመሰሉ ሲሆኑ ሁልጊዜም በ፳፮ ይጀምራሉ በ ፳፭ ደግሞ የሚፈጽሙ ሦስት ወራትን ይይዛሉ። ስለሆነም አሁን የያዝነው መፀው መስከረም ፳፮ ገብቶ ታኅሣሥ ፳፭ ለሐጋይ (ለበጋ) ያስረክባል ማለት ነው። ይህ የመፀው ወቅት በቤተ ክርስቲያን አምስት ወይም ስድስት ሳምንታት የሚኖሯትን ወርኃ ጽጌን ይይዛል። ጽጌም መስከረም ፳፮ ገብታ ጽጌም ኅዳር አምስት ትፈጸማለች። በማግስቱ  ሕዳር ፮  ደግሞ እመቤታችን ከነልጇ በደብረ ቍስቋም ማደሯን እናስባልን። ይህ የአበባ ወቅት ልዩ ልዩ አበቦች መዓዛቸውን ስለሚሰጡ ባለው ምሳሌዊ ትምህርት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መስላ የዘመነ ጽጌን ሥርዓት ሰርታለች። ይህም  እመቤታችን ወደ ግብጽ የተሰደደችውን ስደትና የደረሰባትን መከራ እያሰብን ጥልቅና እጅግ አስደናቂ የነገረ ሥጋዌና ነገረ ማርያም  የነገረ ድኅነትን ትምህርት የምንማርበትና የምናስተምርበት ጊዜ ነው። Read more

‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን›› ቅዱስ ያሬድ

በመጋቢ ሀዲስ ምስጢረ ስላሴ ማና

መስከረም 16 ቀን 2009 ዓ.ም.

‹‹መስቀል ለእለ ነአምን መድኅን – መስቀል ለምናምን መድኒት ነው››። ስለነገረ መስቀሉ ከተናገሩ ሊቃውንት የኢትዮጵያው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ትልቅ ድርሻ አለው። በአምስቱም ድርሰቶቹ በሰፊው ስለ መስቀል ዘምሯል፣ ተናግሯል፣ አመስጥሯል። ከላይ ያነሳነውን ኃይለ ቃል የተናገረውም እርሱ ነው። ምክንያቱም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች ስለ ነገረ ድኅነነት ያጠነጥናሉ። እግዚአብሔር በነገረ ድኅነት ውስጥ ለሰው ልጆች ሁለት የተስፋ መንገዶች ሰጥቷል። አንደኛው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቅዱስ መስቀሉ ነው።

ሁለቱም የተሰጡት የሰው ልጅ ከገነት ሕገ እግዚአብሔርን ጥሶ፣ ትእዛዙን አፍርሶ፣ ዕፀ በለስን በልቶ፣ ከፈጣሪው ተጣልቶ በተሰደደ ጊዜ ነበር። ‹‹በሐሙስ እለት ወበመንፈቃ ለእለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድህክ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ- በአምስት ቀን ተኩል /አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም/ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመስቀሌና በሞቴ አድንኀለሁ›› ቀሌምንጦስ ከልጅ ልጅህ ያለውን ሊቃውንት ‹‹እንተ ይእቲ ማርያም-ይችውም ማርያም ናት›› ብለው ተርጉመውታል። ስለዚህ ሊቃውንቱ ይህ የተሰጠው የሰው ልጅ የመዳን ተስፋ በእለተ ጽንስ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ተጀመረ፤ በእለተ ዓርብ በቅዱስ መስቀል ተፈጸመ ብለው አስተማሩ። ‹‹ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል – የአበው ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ፤ በቀራንዮ መድኃኒት መስቀል ተተከለ›› ብለው ገለጡት። በድርሰታቸው መድኃኒትነቱን ለምናምን መሆኑን ሁላችንም እርግጠኛ መሆን ይገባናል። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ግብረ ዘወሀብከኒ ፈጸምኩ ወናሁ ተፈጸመ ኩሉ- የሰጠኸኝን ሥራ ጨረስኩ እነሆ ሁሉ ተፈጸመ ።›› (ዮሐ 17፥4) ያለው ለዚህ ነበር። ከዚህ የተነሳ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ መስቀሉን ታከብረዋለች፤ ስለ ክብሩ ትናገራለች።

Read more

«መኑ ውእቱ ብእሲ ዘይፈቅድ ሐይወ ወያፈቅር ይርአይ መዋዕለ  ሠናያተ »

በመምህር ፍቃዱ ሣህሌ

ጳጕሜ 5 ቀን 2008 ..

ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው ? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው ?

መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት እንደ ሰውነቱ በርካታ ጥያቄዎችን ጠይቋል። እንደ መንፈስ ቅዱስ ማደሪያነቱ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ለጥያቄዎችም መልስ ሰጥቷል። ከላይ የተቀምጠው ጥያቃዊ  ኃይለ ቃልም በተመሳሳይ ሁኔታ ያቀረበው ጥያቄ ሲሆን ለሁላችንም ጥቅም  ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ላይ አድሮ መልሱን ሰጥቶናል። Read more

ትንሣኤ

በዲ/ን ብሩክ አሸናፊ

ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ..

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ። ነገር ግን ተነሣ የሚለውን ለማመን ሞተ የሚለውን ማመን ስለሚቀድም፥ ጌታችን በዕለተ አርብ መሞቱን የቅዱሳት መጻህፍትን ምስክርነት በማስቀደም እንጀምራለን።

Read more

ኒቆዲሞስ

፩ መግቢያ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ።

እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት የጾመዉ ጾም በመሆኑ ዐቢይ ተብሏል። ማቴ ፬፥፩። እኛም አምላካችን የጾመዉን ጾም ለማስታወስ፥ በረከቱን ለማግኘት፥ እርሱን አርዓያ አድርገን የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን። በዚህ ጾም ከተድላና ከደስታ ወገን ማናቸውንም ማድረግ እንዳይገባና ሁሉም ጿሚ ከሥጋዊ ነገር መጠበቅና መጠንቀቅ እንደሚገባዉ ተጽፏል። ዐቢይ ጾም አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ድኅነተ ዓለም የተቀበለዉን መከራ በማሰብ የምናዝንበት፥ በቸርነቱ በሰጠን ኃይል መንፈሳዊ ከሰይጣንና ከፈቃደ ሥጋ ጋር የምንጋደልበት፥ እኛ በበደልን እርሱ ክሦ እንዳዳነን በማዘከር ደግሞ ወደ ኃጢአት ላለመመለስ ቃል የምንገባበት፥ አብነት ሊሆነን ከኖረልን ሕይወትና ከሠራልን ሕግ የምንማርበትና ለቅዱስ ቁርባን የምንዘጋጅበት እጅግ የከበረ ወቅት ነው። እነዚህ የጾም ዕለታት ለሌሎች ጊዜያት ስንቅ የምንይዝባቸውና ተኩላ ከሆነው ሰይጣን የምንጠነቀቅባቸዉ መሆናችዉም በዓመቱ ዉስጥ ከሚኖሩት ቀናት ሁሉ ልዩ ያደርጋቸዋል።

Read more

“ኦ ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ” ማቴ. ፳፭፥፳፫።

በመ/ ሳሙኤል ተስፋዬ

ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ..

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር ይባላል። ገብር ኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው አስተምሯል። ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐቢይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብር ኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ኄር ጥቂት እንበል።

ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁአለ። ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ። ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “. . . ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛብ፤ . . . በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከብሏል ገላ. ፫፥፰፣ መዝ. ፸፯፥፪

Read more