ትንሣኤ

በዲ/ን ብሩክ አሸናፊ

ሚያዚያ 23 ቀን 2008 ..

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ሲነገር አብሮ የሚነሣው በዕለተ ዓርብ ስለኛ ብሎ የተቀበለው ሞቱ ነው። አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን በፈጸሙት በደል ምክንያት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ሳለ በበደላቸው ንስሐ ገብተው አምላካችንን በመለመናቸው፥ እርሱም የሰው ፍቅር አገብሮት በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ሞቶ ሶስት መዓልት እና ሶስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ። ነገር ግን ተነሣ የሚለውን ለማመን ሞተ የሚለውን ማመን ስለሚቀድም፥ ጌታችን በዕለተ አርብ መሞቱን የቅዱሳት መጻህፍትን ምስክርነት በማስቀደም እንጀምራለን።

Read more

ኒቆዲሞስ

፩ መግቢያ

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የእምነቱ ተከታዮች ሁሉ እንዲጾሟቸው መጀመሪያቸውና መጨረሻቸው ተቀምሮ ጊዜና ወቅት ተወስኖላቸው የተደነገጉ ሰባት የዐዋጅ አጽዋማት አሉ።

እነዚህም አጽዋማት በሐዋርያት ሲጾሙ የቆዩና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና መጻሕፍት የአጿጿም ሥርዓታቸውን የሠሩላቸው ናቸው። ከእነዚህም ሰባት አጽዋማት አንዱና ዋናዉ ዐቢይ ጾም ነው። ይህ ጾም ክብር ምሥጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ፵ መዓልትና ፵ ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት የጾመዉ ጾም በመሆኑ ዐቢይ ተብሏል። ማቴ ፬፥፩። እኛም አምላካችን የጾመዉን ጾም ለማስታወስ፥ በረከቱን ለማግኘት፥ እርሱን አርዓያ አድርገን የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን። በዚህ ጾም ከተድላና ከደስታ ወገን ማናቸውንም ማድረግ እንዳይገባና ሁሉም ጿሚ ከሥጋዊ ነገር መጠበቅና መጠንቀቅ እንደሚገባዉ ተጽፏል። ዐቢይ ጾም አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ድኅነተ ዓለም የተቀበለዉን መከራ በማሰብ የምናዝንበት፥ በቸርነቱ በሰጠን ኃይል መንፈሳዊ ከሰይጣንና ከፈቃደ ሥጋ ጋር የምንጋደልበት፥ እኛ በበደልን እርሱ ክሦ እንዳዳነን በማዘከር ደግሞ ወደ ኃጢአት ላለመመለስ ቃል የምንገባበት፥ አብነት ሊሆነን ከኖረልን ሕይወትና ከሠራልን ሕግ የምንማርበትና ለቅዱስ ቁርባን የምንዘጋጅበት እጅግ የከበረ ወቅት ነው። እነዚህ የጾም ዕለታት ለሌሎች ጊዜያት ስንቅ የምንይዝባቸውና ተኩላ ከሆነው ሰይጣን የምንጠነቀቅባቸዉ መሆናችዉም በዓመቱ ዉስጥ ከሚኖሩት ቀናት ሁሉ ልዩ ያደርጋቸዋል።

Read more

“ኦ ገብር ኄር ወምእመን ዘበውኁድ ምእመነ ኮንከ ዲበ ብዙኅ እሠይመከ” ማቴ. ፳፭፥፳፫።

በመ/ ሳሙኤል ተስፋዬ

ሚያዚያ 1 ቀን 2008 ..

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር ይባላል። ገብር ኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው። ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው አስተምሯል። ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐቢይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብር ኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ኄር ጥቂት እንበል።

ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁአለ። ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ። ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “. . . ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛብ፤ . . . በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከብሏል ገላ. ፫፥፰፣ መዝ. ፸፯፥፪

Read more

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ

መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም.

ደብረዘይት የዓቢይ ጾም እኩሌታ ነው በእለቱም ስለ ዳግም ምጽአት ይነገራል። ስለ ምጽአት ነቢዩ ዘካርያስ «በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉአምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣልአንድ ቀን ይሆናል…. በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይወርዳል።» (ዘካ ፲፬ ) በማለት አስቅድሞ ትንቢት ተናግሯል። አምላክ በዚህ ትንቢት እና በሌሎች ነቢያት ያናገረውን እርሱ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ላይ የዳግም ምጽአት ምልክቶችን እና አመጣጡን ከፍርዱ ሂደት ጋር በግልጽ አስተምሯል። ይህንንም ሁሉ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደብረ ዘይት እለት ስትዘከረው ኖራ በምጽአት ቀን ተስፋዋን መንግሥተ ሰማያትን ትረከባለች:: በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደተለመደው በዚህ የደብረ ዘይት ሳምንት ጽሑፍ ስለ ደብረ ዘይት ስለምጽአት ምልክቶች ስለምጽአት እና ተስፋው እንዘከራለን

Read more

መጻጒዕ (ዮሐ. ፭፥፲፫)

በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

መጋቢት 18 ቀን 2008 ዓ.ም

የነፍሳችንን ማሠሪያ እንዲፈታና ዓለሙን ከተያዘ የኃጢአት በሽታ እንዲያድን ለቤዛነት፤ እንዲሁም የመልካምና የበጎ ምግባራት ሁሉ አብነት ሆኖ በሥራና በቃል እንዲያስተምር ወዳለንባት ምድር በሥጋ ቅድስት ድንግል ማርያም ወረደ ተወለደ:: ቤተክርስቲያናችን በአራተኛው ቢይ ጾም ሳምንት እግዚአ ለሰንበት ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሳይዳየፈጸመውን ተአምራት መጻጒዕ ብላ ሰይማ ስበዋለች። በዕለቱም በዮሐንስ ወንጌል አምስተኛው ምዕራፍ የተቀመጠው ታሪክ በልዩ ልዩ ኅብረ ምሥጢር ተገናዝቦ በሊቃውንቱ ይነገራል።

መጻጒዕ ለ፴፰ ዓመት በአልጋው ላይ ሆኖ ምሕረትን ሲጠባበቅባት የኖረባት ስፍራንቤተ ሳይዳትባላለች በቅዱስ መጽሐፍ የሥፍራዎችን ስያሜ ስንመረምር በይሁዳና በገሊላ ለሚገኙ ሁለት የተለያዩ ግዛቶች በተመሳሳይ አገባብቤተ ሳይዳየሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸው እናገኛለን። በሁለቱ አውራጃዎች (ይሁዳና ገሊላ) ሥርቤተ ሳይዳበሚል የተጠቀሱት ሥፍራዎች በትርጉም ፊደላቱ ያለአገባብ መሰደር ከወለዱት የሞክሼነት ስህተት (Metathetical Corruption) የተገኘ ክፍተት እንጂ ቦታዎቹስ በጥንታዊቷ የእስራኤል ግዛት ከመገኘታቸው ውጪ ምንም የሚያገናኛቸው መልክአ ምድራዊ ኩነት የለምጲላጦስ ጰንጤናዊ መልአከ ይሁዳ ወሄሮድስ ንጉሠ ገሊላ” (ሉቃ· ፫፥፩) እንዲል የግዛቶቹ አገረ ገዢዎችም እንዲሁ ለየቅል ነበሩ። አገባቡን አካቶ ለመረዳት እንዲያመች የሁለቱንም መካናት ከተማና መንደር ለይቶ ማወቁ ተገቢ ነው።

Read more

ምኵራብ

ቀሲስ ኃይለኢየሱስ ተመስገን


መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም

ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል ድህረ ዓለም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መለወጥ ሳያገኛት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከስጋዋ ስጋ ከነፍ ነፍስ ነስቶ የተወለደ ወልደ እግዚአብሔር ወልደ ማርያም በተዋህዶ ከበረ“ይደልዎነ ንምን ከመ ቦቱ ለወልደ እግዚአብሔር ክልኤቱ ልደታት ቀዳማዊ ልደቱ እም እግዚአብሔር አብ እምቅድመሉ መዋዕል ወዳግማዊ ልደቱ እም እግእዝትነ ቅድስት ድንግል ማርያም በደራዊ መዋዕል” ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ክፍል ብለን በማመን እንደ አባቶቻችን ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን ስለ ምኵራብ እንማራለን የምናነበውን ለበረከት ያድርግልን አሜን።

Read more

ዘወረደ

ዲያቆን ስመኘው ጌትዬ

የካቲት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.

እንኳን ለዓቢይ ጾም በሰላም አደረሰን። የ፳፻፰ (2008) . ዓቢይ ጾም የካቲት ፳፰(28) ቀን ተጀምሮ ሚያዝያ ፳፫ (23) ቀን ይፈጸማል። ይህ ጾም 8 ታላላቅ ሳምንታት የተከፋፈለ ሲሆን እነርሱም ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኲራብ፣ መጻጒዕ ደብረዘይት፣ ገብርኄር፣ ኒቆዲሞስ፣ እና ሆሳዕና ይባላሉ፡፡ በዚህ ጾም ውስጥ በአጠቃላይ ጾመ እግዚእነ (የጌታችን ጾም) አርባውን ቀን ሲይዝ የመጀመሪያው ሳምንት ጾመ ሕርቃል እና የመጨረሻው ሳምንት የጌታን ሕማማት የምናስብበት ሰሙነ ሕማማት የቀረውን ክፍል ይይዛሉ፡፡

ዛሬ የመጀመሪያውን ሳምንት ወይም ዘወረደ የተባለውን ጾም ስያሜውን እና ምስጢሩን በታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ትምህርት እንዴት እንደተገለጠ እናያለን፡፡ የብሉያት እና የሐዲሳት መጽሐፍት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከጸዋትወ ዜማ መጽሐፍቱ አንዱ በሆነው የድጓ ክፍል ጾመ ድጓ (በጾም ስለሚደረስ ጾመ ድጓ ተብሏል) ስለ ጾም ብዙ ጽፏል።ከዘወረደ ጀምሮ ያሉት ስምንቱም ሳምንታት ስያሜያቸውን ያገኙት ከጾመ ድጓ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ ይህ የዜማ መጽሐፍ በተለይ ዋዜማ ክፍሉ ላይ ያሉትን የመጀመሪያ ቀለማት በመምረጥ የየሳምንታቱን ስያሜዎች አስገኝቷል፡፡ በዘወረደ ድርሰቱ ቅዱስ ያሬድ በጾም ልናስባቸው እና ልናከናውናቸው የሚገቡንን ነገሮች ከሥነምግባር፣ ከጸሎት፣ ከቤተክርስቲያን፣ ከመስቀሉ አንፃር እየሆነ ይነግረናል፡፡ ዛሬ በዘወረደ ድርሰቱ ከተገለጡት በጥቂቱ እያነበብን እንማማራለን።

Read more

የገና በዓል በቅዱስ ላሊበላ

በቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ

ታህሳስ 27 ቀን 2008 ዓ.ም

በቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን በድምቀት ከሚከበሩት የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓበይት በዓላት መካከል ገና (የልደት) በዓል አንዱ ነው።ይህ በዓል ሰማይና መሬት የታረቁባት፣ ሰው እና መላእክት በአንድነት የዘመሩበት ከሁሉም በላይ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲጠበቅ የነበረው የአዳም ተስፋ የተፈፀመበት፣ አምላክ የአምላክ ልጅ በግሩም ተዋህዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደበት ታላቅ የደስታ ቀን ነው።

Read more

ጾም በስደት ሀገር

በቀሲስ ለማ በሱፈቃድ

ሐምሌ 30 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሰባት አጽዋማት አሉ :: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሰታ ነው:: ጾም ማለት በታወቀ ወራት ሳምንታት እና ዕለታት እስከ ጾሙ ፍጻሜ ድረስ ከተከለከሉ ጥሉላት ምግቦችና መጠጦች ወይም የእንስሳት ውጤቶች ሥጋ ወተትና ከመሳሰሉት መከልከል ሲሆን፣ ከዚያ ውጪ የሆኑ ምግቦች ለተወሰነ ሰዓት ብቻ መከልከል ነው :: ‘’ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም’’ /ዳን .. /። ‘’ጾምሰ ተከልዖተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ እውቅ ‘’ /ፍትሐ ነገሥት አንቀጸ ጾም ተመልከቱ/። በሌላ መልኩ ደግሞ ጾም ማለት በዓይናችን በእጃችን በእግራችን በአንደበታችንና በመሳሰሉት የሰውነት ክፍሎቻችን ሁሉ ሳይቀር የምንጾመው ነው:: “ስንጾም አንደበታችንም ከማይገቡ ንግግሮችና ከነቀፋዎች ይጹም::’’ /.ዮሐንስ አፈ ወርቅ በእንተ ምክንያተ ሐውልታት ፫ ;.፲፪”/:: ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው «ይጹም ዐይን፥ ይጹም ልሳን፥ ዕዝንኒ ይጹም እምሰሚዐ ህሱም በተፋቅሮ፤ በፍቅር በመጽናት ዓይን ክፉ ነገርን ከማየት ይጹም፣ አንደበትም ክፉ ከመናገር ይጹም፣ ጆሮም ክፉ ከመስማት ይጹም” ብሎ ገልጾታል።

Read more

ዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር

ሚያዚያ 30 ቀን 2007 ዓ.ም.

በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ማኀበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማዕከል የጀርመን ቀጣና ማዕከል በሙኒክ ከተማ በደ/ብ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግንቦት 15 እና 16 ቀን 2007ዓ.ም (May 23 – 24/2015) የዐውደ ርእይ እና የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር አዘጋጅቷል። በዕለቱ የሚኖረውን ዝርዝር መርሐ ግብር ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ።

alt

ቀ/ማዕከሉ በሙኒክ ከተማ እና አካባቢዋ ለሚገኙ ምዕመናን በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ጊዜያቸውን አመቻችተው ይህን መርሐ ግብር እንዲሳተፉ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ አስተላልፏል።

ወስብለእግዚአብሔር!