በአውሮፓ የወላጆች የውይይት መድረክ

ሚያዚያ 22 ቀን 2007 ዓ.ም.

በአውሮፓ በአይነቱ ልዩ የሆነ የወላጆች የውይይት መድረክ «ሕጻናትን እና ታዳጊዎችን እንዴት ማሳደግ አለብን» በሚል ርዕስ ሚያዝያ 27 (May 5, 2015 GC) ቀን 2007ዓ.ም ከምሽቱ 20፡00 ሰዓት CET በፓልቶክ ይካሄዳል። እባክዎን ዝርዝር መርሃ ግብሩን ከማስታወቂያው ላይ ይመልከቱ።

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ

መጋቢት 4 ቀን 2007 ዓ.ም.

ደብረዘይት የዓቢይ ጾም እኩሌታ ነው ። በእለቱም ስለ ዳግም ምጽአት ይነገራል። ስለ ምጽአት ነቢዩ ዘካርያስ «በዚያን ቀን እግሮቹ በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ላይ ይቆማሉአምላኬ እግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር ይመጣል አንድ ቀን ይሆናል…. በዚያም ቀን የሕይወት ውኃ ከኢየሩሳሌም ይወጣል፤ እኩሌታው ወደ ምሥራቁ ባሕር እኩሌታውም ወደ ምዕራቡ ባሕር ይወርዳል።» (ዘካ ፲፬ ፥ ፬) በማለት አስቅድሞ ትንቢት ተናግሯል :: አምላክ በዚህ ትንቢት እና በሌሎች ነቢያት ያናገረውን ፣ እርሱ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ ላይ የዳግም ምጽአት ምልክቶችን እና አመጣጡን ከፍርዱ ሂደት ጋር በግልጽ አስተምሯል። ይህንንም ሁሉ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በደብረ ዘይት እለት ስትዘከረው ኖራ በምጽአት ቀን ተስፋዋን መንግሥተ ሰማያትን ትረከባለች:: በመሆኑም በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደተለመደው በዚህ የደብረ ዘይት ሳምንት ጽሑፍ ስለ ደብረ ዘይት ፣ ስለምጽአት ምልክቶች ፣ ስለምጽአት እና ተስፋው እንዘከራለን ።

Read more

የልጆች አስተዳደግ በውጭው ዓለም*

በላቸው ጨከነ (ዶ/ር)

የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም.

ልጆች ብዙ ተባዙ” ሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ከእግዚአብሔር የሚገኘ በረከቶች ናቸው ቅዱስ ዳዊት ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናችው(መዝ ፻፳፮) እንዳለ። ቅዱሳን ጻድቃን፣ ጳጳሳት ካህናት፣ ነገሥታት እና መሣፍንት የሚገኙት ከዚሁ አምላካዊ በረከት ነው። በአለንበት ዘመን የአኗኗር ዘይቤ መቀየር ፣ የኑሮ ጫና እና የዓለም መቀራረብ የልጆችን አስተዳደግ ለሁሉም ወላጆች እና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ፈታኝ አድርገውታል። በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ወላጆች ለሚኖሩበት ሀገር ባህል እና ሕግ እንግዳ ስለሚሆኑ ከቤተ ዘመድ ስለሚርቁ ፣ የስራ ጫና እና የጊዜ እጥረት ስለሚያጋጥማቸው የዓለም ነጋዴዎች ልጆችን ከሃይማኖትና ከሥነ ምግባር የሚያስወጡ ተለዋዋጭ ሸቀጦችን ስለሚያጐርፉና እለት እለት ለመሳለም የሚሿት ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅርባቸው እንደልብ ስለማትገኝ የልጆችን አስተዳደግ የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዘመኑን ዋጅቶ ልጆችን በሀይማኖትና ግብረ ገብ ትምህርት ለማሳደግ ከወላጆች ብዙ ይጠበቃል።በዚህ ጽሑፍ የቀደሙ ወላጆችን የልጅ አስተዳደግ ከቅዱሳት መጻሕፍት ለአብነት አይተን በስደት ስንኖር ልጆቻንን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን በሰፊው እንዳስሳለን።

Read more

ጾመ ነነዌ

ኤርምያስ ልዑለቃል (ዶ/ር)

ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም. 

የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡” (ማቴ ፲፪፥፵)

ይህንን የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን ለዚህ ትምህርቱ መነሻ ያደረገው የጻፎች የፈሪሳውያንን ጥያቄ ነው፡፡መምህር ሆይ ከአንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን” ቢሉትክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሌሊት አንደነበረ የሰው ልጅም በምደር ልብ ሦስት ቀንና ሌሊት ይሆናል፡፡የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዳሉ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡ እነሆ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ” ብሏቸዋል፡፡ (ማቴ ፲፪፥፵) ጻፎችና ፈሪሳውያን ምልክት መጠየቃቸው ይገርማል! የተሰጣቸውን ምልክት ሳይጠቀሙ እና በሚያዩአቸው ተአምራት ሳያምኑ ሌላ ምልክት መሻታቸው ይደንቃል! አልተረዱትም እንጂ የእርሱ በመካከላቸው መገኘት በራሱ ምልክታቸው ነበረ::ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋልእነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” አንዳለ ነቢዩ (ኢሳ ፲፬ ) ሰማያዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ያበሰራት እመብርሃን ምልክታቸው ነበረችበድንግልና ጸንሳ በድንግልና የወለደች መቤታችን ምልክታቸው ነበረችበጌታችን ልደት ወደ ቤተልሔም ወርደው የዘመሩ ቅዱሳን መላእክትም ምልክቶቻቸው ነበሩየተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው” እያሉ የመጡት ሰብአ ሰገልም ምልክቶቻቸው ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ በመካከላቸው ሆኖ ማየት ለተሳናቸው ዓይን ሲሰጥ መስማት የተሳናቸው እንዲሰሙ ሲያደርግ ለምጻሞችን ሲያነጻ እና ሙታንን ሲያስነሳ እያዩ እንደገና ሌላ ምልክት አምጣ ማለታቸው የሚገርም ነው! ለዚህም ነውክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን ይሻል” ብሎ ወደ ነነዌ ሰዎች ትምህርት የወሰዳቸው፡፡

ነነዌ ማናት?

Read more

ጥምቀት እና በዓለ ጥምቀት

በዲ.ን ዶ.ር አለማየሁ ኢሳይያስ

ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም.

ጥምቀት

ጥምቀት የሚለው ቃል አጥመቀ (አጠመቀ ወይም ነከረ) ከሚለው የግእዝ ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም መጠመቅ ፣ መነከር ፣ መደፈቅ ፣ ውኃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው ። ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ላይ የሚፈጸም ምሥጢር ሲሆን ያለ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሳተፍ አይቻልም ። (ዮሐ. ፪፥፩-፵፩) በጥምቀት ከእግዚአብሔር በመንፈስ እንወለዳለን፤የልጅነት ፀጋንም እናገኛለን። የነፍስ ድኅነትን ለማግኘትም በጥምቀት የእግዚአብሔርን ልጅነት ማግኘት ግድ ነው ።(ማር ፲፮፥፲፮ ፤ ዮሐ ፫፥፭) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን እለት በታላቅ ድምቀት በየዓመቱ ጥር ፲፩ ቀን እንደምታከብር ይታወቃል። የጥምቀት በዓል አከባበር የሚጀምረው ጥር ፲ ቀን በጾም ሲሆን ይህም እለት ገሀድ በመባል ይታወቃል።ትርጉሙም መገለጥ ማለት ነው። ምክንያቱም ወልድ የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ ፣ በኋለኛው ዘመን ደግሞ ያለ አባት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሆኖ ተዋሕዶ ስለተገለጠልን እና በ፴ ዓመቱ በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ተጠምቆ ክብሩንና ጌትነቱን ስለገለጠልን ነው።

Read more

ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ

ዲ.ን ብሩክ አሸናፊ

ቀን ታህሣስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም.

«ኦ ዝ መንክር ልደተ አምላክ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ» ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ

ይህ ቃል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ በሜሶጶጣሚያ ውስጥ በምትገኘው በንጽቢን ተወልዶ፣ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስኪል ድረስ ጸጋ እግዚአብሔር በዝቶለት እጅግ ብዙ ድርሳናትን የደረሰው፣ በጉባኤ ኒቅያ መምህሩ ከነበረው የንጽቢን ጳጳስ ያዕቆብ ጋር የተገኘው፣ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እመቤታችንን ባመሰገነበት ውዳሴ ማርያም በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ልዩ እና ድንቅ የሆነውን የጌታችንን ልደት አድንቆ በሐሙስ ክፍል ላይ የጻፈው ነው።

Read more

«ትንቢት ይቀድሞ ለነገር ፤ ተግባርን (ድርጊት) ትንቢት ይቀድመዋል»

በዘመናት ውስጥ ለእግዚአብሔር ምስክር ሆነው ሕይወታቸውን ከሰጡ ሰዎች መካከል ሠለስቱ ደቂቅ በዚህ ዘመን በተለይ ለወጣት ክርስቲያን ልጆች አርአያ ሆነው ይጠቀሳሉ። እግዚአብሔርም እራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው ስለእርሱ በመስጠት የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ፤ ከእጅህም ያድነናል። ”(ዳን 316) በማለት እንደተናገሩት ትንቢት ፣ በቅጽበት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ ተአምራቱን ገልጾላቸዋል። በእውነትም ይህ ታሪክ በተለይ በሃገራችን በታላቅ በዓል ታጅቦ መከበሩ እግዚአብሔርን በእውነት ላመኑ ፣ በሥሙም ለታመኑ ፣ ወደፊትም አምነው ለሚታመኑ ሁሉ ትልቅ ምስክር ነው ።

የቅዱስ ገብርኤል በዓል ታሪካዊ አመጣጥ

Read more

አቡነ መብዓ ጽዮን (በ፲፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን)

ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም

መብዓ ጽዮን በ፲፭ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ልጅ በማጣታቸው በጾምና በጸሎት ፈጣሪያቸውን ከሚለምኑ ባልና ሚስት ተወለዱ። የንቡረ እድ ሳሙኤል ረባን የሆነው መብዓ ጽዮን አባቱ እስከ ዳዊት ያለውን ትምርት አስተማረውና ዲቁናን ተቀበለ። ልጁ የትምህር ዝንባሌ እንዳለው አባቱ ተረድቶ ቤተ ማርያም ከሚባለው ደብር ወስዶ ተክለ አማኅ ከሚባል የቅኔ መም ዘንድ አስገባው። በዚያም ቅኔና እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን እውቀቶችን ገበየ። ከዚህም በተጨማሪ ሥዕል መሳልና ጽሕፈት መጻፍ ተማረ። መብዓ ጽዮን የልጅነቱን ዘመን ሲፈጽም ‹‹ለነፍሳቸው ድኅነት ዋጋ ያገኙ ቅዱሳን ብዙ ናቸው።በመጾም ያገኙ አሉ፤ በትምርት ያገኙ አሉ፤ በድካም ያገኙ አሉ፤ በጸሎት በትጋት ያገኙ አሉ፤ እኔ ግን የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን የሞቱን መታሰቢያ ማድረግ ይገባኛል። በዚህም ፊቱን አያለሁ፤ እርሱ ጌታ ለደቀመዛሙርቱ ‹‹የትንሣኤዬን መታሰቢያ ብታደርጉ የሞቴን መታሰቢያ አድርጉ›› ብሏልና›› በማለት ፍላጎቱ በምንኩስና በመኖር ፈጣሪን ማገልገል መሆኑን ለወላጆቹ ገለጸላቸው።

Read more

አብርሃ ወአጽብሐ

ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም

ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሐ አባታቸው ታዜር እናታቸው ሶፍያ/አህየዋ/ በቅድስና የሚኖሩ እግዚአብሔርን በቅድስና በንጽህና የሚያገለግሉ ነገር ግን ልጅ ያላገኙ መካኖች ነበሩ። ስለሆነም ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህ በትእዛዝህም የሚኖር ልጅ ስጠን እያሉ እግዚአብሔርን ይለምኑ ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ስለ እግዚአብሔር ቸርነት ሲነጋገሩ ንግሥት ሶፍያ የሐና እመ ሳሙኤልን ጸሎት በመጥቀስ እሷም እንደ ሐና ሱባዔ ገብታ ፈጣሪዋን እንድትለምን ንጉሡን ጠየቀችው፤ ንጉሡም ኦ ብእሲቶ ሰናየ ሀለይኪ- አንቺ ሆይ መልካም አስበሻል በማለት በምክሯ ተስማምቶ ሱባዔ ገብታ ፈጣሪዋን በጸሎት እንድትጠይቅ ፈቀደላት፡፡ ንግሥት ሶፍያም የካቲት 18 ቀን ሱባዔ ገብታ ፈጣሪዋን መለመን ጀመረች፡፡ ከጸሎቷም ጥቂቱ «በኪሩቤል ላይ የምትኖር፣ ቀለያትንም (ጥልቅ ባሕርንም) የምትመለከት ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ አቤቱ ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ፤ ልቅሶየንም አድምጥ ቸል አትበለኝ» የሚል ነበር፡፡

Read more

«የአክለክሙ መዋእል ዘሃለፈ ፥ ያለፈው ዘመን ይብቃችኋል» ቅዱስ ያሬድ እና ፩ኛ ጴጥሮስ ፬ ፥ ፫- ፬

በመጋቢ ሀዲስ ምስጢረ ስላሴ ማናየ

ጳጉሜን  ፭ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. 

«የአክለክሙ መዋእል ዘሃለፈ ፥ ያለፈው ዘመን ይብቃችኋል» ቅዱስ ያሬድ እና ፩ኛ ጴጥሮስ ፬ ፥ ፫- ፬

በቅድሚያ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ ያሸጋገረን፤ በመግቦቱ ያልተለየን፤ በችርነቱ የጠበቀን፤ በምህረት አይኖቹ የተመለከተን፤ በብርቱ ክንዶችሁ የደገፈን፤ የዘመናት ባለቤት የፈጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ለዚህ ኣመት ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ይድረሰው አሜን።

በቸር አድረን የምንውለው፤ ተኝተን የምንነሳው፤ ሰርተን የምናገኘው፤ ደክመን የምንበረታው፤ ታመን የምንደነው፤ ወድቀን የምንነሳው፤ ከቸርነቱ ከጠባቂነቱ የተነሳ ነው። እግዚአብሔር አምላካችን ሰውን ከድንጋይ እና ከእንጨት ለይቶ በደማዊት ነፍስ ከእንስሳት እና ከአራዊት ለይቶ በህያው ነፍስ አክብሯታል በአርያው እና በአምሳሉም ፈጥሯታል። «ወገብሮ እግዚአብሔር ለእጓለ እመህያው እመሬተ ምድር በአሪያሁ ወበአምሳሊሁ ፤ እግዚብሔር አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአርያውና በአምሳሉም ፈጠረው» ዘፍ ፩፥፪፮

Read more