ሥነ-ፍጥረት/ለልጆች

ነሐሴ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. 

ልጆች እግዚአብሔር አምልካችን ሰማይ እና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው የሚኖሩትን ፍጥረታትን መቼ እንደፈጠራቸው ታውቃላችሁ? በዚህ ጽሁፍ ስለ ሥነ-ፍጥረት ትማራላችሁ።

እግዚአብሔር ፍጥረታትን ካለመኖር ወደመኖር ያመጣ የሁሉ ፈጣሪ ነው። እግዚአብሔርም በሳምንት ውስጥ ካሉ ሰባት ቀናት (ዕለታት) በመጀመሪያዎቹ ስድስት ቀናት የተለያዩ ፍጥረታትን ፈጠረ።

     kids1

Read more

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

መግቢያ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በተለያየ ጊዜ ካህናት እና ምእመናን የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት በተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባ ድርሻቸውም ምን እንደሆነ ያስተምራቸው ነበር:: ለምሳሌ የመንፈስ ልጁ የሆነ ቅዱስ ጢሞቴዎስን በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት ሲኖር ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲህ በማለት መክሮታል:-“በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዐምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው::” (1ጢሞ 3፥15)

Read more

እንደተናገረ ተነሥቷል (ማቴ28፥5)

እንኳን ለጌታችን፣ ለአምላካችንና ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን።

በአባ ወልደትንሣኤ ጫኔ

ሚያዚያ 26 2005ዓ.ም.

Easterጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በከብቶች በረት ከተወለደበት ሰዓት ጀምሮ ለሰው ልጅ ድህነት ሲል ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በጲላጦስ ካለበደሉ ከወንበዴዎች ጋር ተፈርዶበት፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጥቶ አዳምንና ዘሩን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መልሶ በሦስተኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብርሃንን ተጎናጽፎ  በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል።

Read more

ደብረ ዘይት

በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ

መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም. 

  

የዓለሙ ፍጻሜ ምልክቱ ምንድ ነው?/ማቴ. 24፣3/

 

በዓቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት ደብረ ዘይት 5ኛው ሳምንት ላይ ይውላል፡፡ ደብረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ ዛፍ ተራራ ማለት ሲሆን፣ ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ ቅዱሳን ሐዋርያት” የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?”/ማቴ. 24፣3/ ብለው ጠይቀውት እርሱም የማይቀረውን የዓለም ፍጻሜና አስቀድመው የሚፈጸሙ ምልክቶችን አስረድቷቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ በደብረ ዘይት ሳምንት ታስበዋለች፤ ለምእመናኑም ከዘመኑ ሁኔታ አንጻር በመጻሕፍት የተጠቀሱትን የትንቢት ምልክቶቹን ከተግባራዊ የዓለም ክንዋኔዎች አንጻር በማገናዘብ ታስተምራለች፡፡ በመሆኑም በቤተ ክርስቲያናችን በደብረ ዘይት ሳምንት ምጽአትን አስመልክቶ የሚነገሩ ምስጢራት እጅግ ሰፊ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጽሑፍ በመጠኑ የምናየው ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር በዓለም እየተከሰቱ ካሉ ወቅታዊ ምልክቶች ጋር በማገናዘብ ይሆናል፡፡

Read more

መንፈሳዊ ሕይወትና ስደት

በይበልጣል ጋሹ

የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዚህ አጭር ጽሁፍ ዓላማ በተለያየ ምክንያት በስደት ለምንኖር የቦታ መቀየር ተፅዕኖ ሳያሳድርብን በሃይማኖታችን ጸንተን እስከመጨረሻው በመንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖርና እግዚአብሔር አምላክ ሁልጊዜ ከስደተኞች ጋር መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ተገንዘበን “እግዚአብሔር ስደተኞችን ይጠብቃል” መዝ 145፡9 የሚለውን ህያው ቃል በውስጣችን አስቀምጠን የሚመጣብንን ፈተና ሁሉ በእግዚአብሔር እንደምንወጣው ለማስረዳት ነው።

ነብዬ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለው? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፣ እስከ ባሕህር መጨረሻም ብበር በዚያ እጅህ ትመራኛለች ቀኝህም ትይዘኛለች። በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል ሌሊት በዙርያ ብርሃን ትሆናለች” መዝ 138፡7-11  ብሎ  እንዳስተማረን የሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር በማንኛውም ቦታ፣ ጊዜ፣ ስዓትና ሁኔታ በምህረቱ፣ በቸርነቱ፣ በይቅርታውና በርኅራኄው እየጎበኘ በመንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር በምንሄድበት ሁሉ ጠብቆቱ አይለየንም።

Read more

“እውነት እውነት እልሀለሁ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።” ዮሐ ፫፡፭

በይበልጣል ጋሹ

ጥር ፲ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.

timiket 2005ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስጋዌው በምድር በነበረበት ዘመን ከፈጸማቸው እና ለሰው ልጅ ከሰጣቸው ሚስጢራት  አንዱ ጥምቀት ነው። “ጥምቀት” የሚለው ቃል አጥመቀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም፣ መነከር፣ መዘፈቅ፣ መደፈቅ፣ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነዉ። በሚስጢራዊ ትርጉም ደግሞ ብዙ ምሳሌዎች አሉት። ከምሳሌዎች መካከልም፦ የአብርሃም ከሃገሩ መውጣትና ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ከነዓን መግባት የጥምቀት ምሳሌ ነው። ምዕመናን ከዓለመ ኃጢአት ወጥተው የመንግሥተ ሰማያት ዜጎች የሚሆኑት በጥምቀት ነውና። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በ፩ጴጥ ፫፡፳፩ ላይ ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነባትን መርከብ የጥምቀት ምሳሌ ናት ብሏታል ምክንያቱም ምዕመናን ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ስለሆነ።  እንዲሁም ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ቆሮ ፲፡፩ እስራኤል ከግብፅ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባሕር ተሻግረው ወደ ምድረ ርስታቸው ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀት ምሳሌ አድርጎ  ተናግሯል፤ምእመናን ባሕረ ኃጢአትን ተሻግረው ምድረ ርስት መንግሥተ ሰማያት የሚወርሱት በጥምቀት ነውና። ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት፣የቤተ ክርስቲያን አባል የምንሆንበት፣ የኃጢያት ስርየት የስጋ ፈውስ የምናገኝበት ረቂቅ ምስጢር ነው።

ሕፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውኅበ ለነ፤ ሕፃን ተወለደልን ወንድ ልጅም ተሰጠን፡፡ ኢሳ 9፣6 (ውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ)

ዲ/ን ውብዓለም ደስታ

ታኅሣስ ፳፰ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.

lidet-2005

አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ተላልፎ አትብላ የተበለውን ዕፀ በለስ በልቶ በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ፤ በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ከገነት ከወጣ በኋላ፤ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ፤ ገነትን ታህል ቦታ አጥቼ ቀረሁን እያለ ሲያዝን፤ ጌታ ኀዘኑን አይቶ ልመናውን ሰምቶ ‹‹በኀሙስ እለት ወበመንፈቃ ለእለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ፣ ወእትቤወከ በመስቀልየ ወበሞትየ፤በአምስት ቀን ተኩል ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በመስቀል ተሰቅዬ በሞቴ አድንሀለሁ›› መጽሐፈ ቀለሜንጦስ፤ ብሎ ቃል ገብቶለት ነበር፡፡ ጊዜውም ሲደርስ አውጉስጦስ ቄሳር ዜጎቹን ለመቁጠር ፈልጎ ወደ ትውልድ አከባቢያቸው ሂደው እንዲቆጠሩ አዘዘ፡፡ መጽሐፍ ‹‹ወወጽአ ትእዛዝ እምኀበ አውጉስጦስ ቄሣር ከመ ይጸሐፍ ኩሉ ዓለም›› (ሉቃ 2፡1) እንዲል፡፡ ጌታም ከዘመኑ ዘመን፣ ከወሩ ወር፣ ከዕለቱ ዕለት ሳያሳልፍ በጽኑ ቀጠሮው ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን በኅቱም ድንግልና ተጸንሶ፤ በኅቱም ድንግልና በቤቴልሔም የእንግዳ ማረፊያ አልነበራቸዉምና በከብቶች በረት ተወለደ፡፡

Read more

ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ

አባቷ  ባሕር አሰግድ እናቷ  ደግሞ  ክርስቶስ አዕበያ  ይባላሉ። ትውልዷ ከዳሮ /ምስራቅ ኢትዮጵያ/ ወገን ነው። ወንድሞቿ ዮሐንስና ዘድንግል በንጉሥ  ሱስንዮስ ጊዜ ታላላቅ ባለስልጣናት ነበሩ። እናት አባቷ  በህግ በስርዓት ካሳደጓት በኋላ ሥዕለ ክርስቶስ የሚባል የስስኑዮስ የጦር አበጋዝ ቢትወደድ  አግብታ 3 ልጆች መውለድዋን ገድሏ ይናገራል። ይህ ቢትወደድ ይኖርበት የነበረው ግንብ ቤት ፍራሽ እስከ አሁን ድረስ በጋይንት ስማዳ ይታያል።

Read more

በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል (ማቴ. 6፣4).

በዲ.ን ኃይሉ ተረፈ

ኅዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም.

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባዉና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኅቡዕ በምንፈጽማቸዉ ሥራዎች ሁሉ እዉነተኞች ተጠቃሚዎች እንድንሆን ሥራዎቻችን ሁሉ በእርሱ ዘንድ ሚዛን የሚደፉና የሚታዩ እንዲሆኑ “በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከልሃል”  (ማቴ. 6፣4) በማለት ይመክረናል፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ያላዩትን ሁሉ የሚያይ፣ በሰዎች ዘንድ ዋጋ ያልተሰጠዉን እርሱ ግን ዋጋ የሚሰጠዉ፣ ለሁሉም እንደ ሥራዉ የሚከፍል እዉነተኛ ዳኛ ስለሆነ ዛሬ ለምንፈጽማቸዉ ክርስቲያናዊ ሥራዎች በግልጥ እንደሚከፍለን ደጋግሞ አስተምሮናል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ም.25፣31 ጀምሮ እስከ መጨረሻዉ ያለዉን ስንመለከት  ሰዎች ለሠሩት ለበጎዉ ሥራቸዉ የዘላለም ሕይወትን፤ ለክፉ ሥራቸዉ ደግሞ የዘላለም ኩነኔን በግልጥ እንደሚቀበሉ እንገነዘባለን፡፡

Read more