የጀርመን ንዑስ ማእከል አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት አካሄደ
በጀርመን ንዑስ ማእከል
ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም.
የጀርመን ንኡስ ማእከል ከመጋቢት ፲፯ እስከ መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም አራተኛውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በጀርመን የግብፅ አቡነ እንጦንስ ገዳም አካሄደ፡፡ በዚህ ሐዊረ ሕይወት ከጀርመን እና ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን የተሳተፉ ሲሆን በጠቅላላ የተጓዦች ብዛት 250 ነበር። የጕዞ መነሻውን መጋቢት ፲፯ ከቀኑ 11 ሰዓት ከፍራንክፈርት ዋናው ባቡር ጣቢያ በማድረግ ወደ ገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል ጉዞ በባቡርና ከዛም የቻለ በእግር የ30 ደቂቃ መንገድ በመጓዝ ወደ ገዳሙ ተደርሷል። በተዘጋጀው መርሐ ግብር መሠረት ዓርብ ምሽት በመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ አባተ “የሕይወት ጉዞ” በሚል ርዕስ ትምህርት ለመእመናን ተሰጥቷል። በመቀጠልም ቅዳሜ ጠዋት 11፡30 ኪዳንና ቅዳሴ እንደሚኖር ማሳሰቢያ ከተሰጠ በኋላ የዕለቱ መርሐ ግብር በጸሎት ተዘግቷል። Read more